የኢሬቻ የሠላም የሽልማትና የኢሬቻ ባህል በደማቅ ስነ ስረዓት ተከበረ 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ከባህል ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የኢሬቻ ሠላም የሽልማት በደማቅ ስነስርዓት በማዕከሉ አዳረሽ መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም ለሠላም ለተጉ ሰዎች የእውቅና ሽልማት በመስጠት ተክበረ፡፡

በእለቱ የኢሬቻን ባህል አከባበር የሚያስቃኝ የጥናት ጹሁፍ የቀረበ ሲሆን ባህሉን የሚያመለክቱ የባህልዊ ውዝዋዜ እንዲሁም የአባገዳዎች ምርቃት ቀርቧል፡፡

ከግራወደቀኝ ተዳሚዎች ምርቃት ሲቀበሉና የአባገዳዎች ምርቃት ሲሰጡ 

የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ እርሳና ሊቃነ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ እና ብጹዕ አቡነ ማቲዎስ፣ሼክ ኡመር፣ አባገዳ በየነ ሰምበቶ፣አርቲስት ማህሙድ አህመድ፣አንጋፋ አርቲስት የኦሮሚኛ ዘፈን ተጫዋች አሊ ቢራ፣ዶ/ር ሰአሊ ለማ ጉያ፣የሱማሌ ክልል ሰለም የሠሩ መህመድ አህመድ እና የጋሞ ሀገር ሽማግሌዎች(ካዎች) ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የኢሬቻ የሠላም ሽትልማት ተሸላሚዎች በከፊል 

በእለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባህና ቱሪዝም ሚኒስቴር ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ፎዚያ አሚን እንዳሉት ዛሬ ለደረስንበት ሠላም አባገዳዎች፣ቄሮች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣የእመነት

አባቶች ትልቅ መስዋትነት እንደከፈሉ አስታወስው ሽለማቱን ለመስጠት ያስፈለገበትም ይህን ሥራ ለማመስገንና የህን ባህላዊ ግጭት አፈታት ስርዓት ለማጠናከርና አውቅና ለመስጠት መሆኑን ተናግረዋል፡ 

ከግራ ወደቀኝ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ፎዚያ አሚን ንግግር ሲየደርጉና የጋሞ ወጣቶች ንግግር ሲከታተሉ

ሚኒስትሯ ለተሸለሚዎቹን እንኳን ደስ አላችሁ መልእክት በማስተላለፍ የሽልማት ስነስርዓት ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ አክለውም እንደዚህ ለሀገር ሠላም አንድነት የሠሩና የሚሠሩ አካላትን በማበረታታት ባህላችን ለዓለም የማስተዋወቅ ሥራ በሰፊው እንደሚሠራ ቃል ገብተዋል፡፡

የኢሬቻን በዓል አከባበር አስመልክቶ አቶ ስንታየሁ ቶላ የጥናት ጹሁፍ ያቀረቡ ሲሆን ኢሬቻ በዓል በሁለት ተከፍሎ በመስከረም ወርና በበጋ ወር ማብቂያ በምስጋና በምልጃ እንደሚከበር ተናግረዋል፡፡

ከግራ ወደቀኝ አቶ ስንታየሁ ቶላ የጥናት ጹሁፍ ሲያቀረቡና ታዳሚዎች ሲከታተሉ

የጥናት ጸሁፍ አቅራቢው እንዳሉት በበዓሉ የአሮሞ ህዝብ የሚያምንበትን ሰማይን፣ምድርን ሁሉንም ነገር የፈጠረ እንድ ጥቁር አምላኩን ዝናብ እንዲሰጠው በበጋ ወራት መጨረሻ ላይ የሚማጸንበት፤ዝናብ ስላዘነበለትና መስኩን ለምለም ስላደረገለት ደግሞ በመስከረም ወር መጨረሻ ላይ የሚያመሰግንበት ባህል መሆኑን አብራርተዋል፡፡በኢሬቻ በዓል ሀብታም ሳይል ደሃ በመድብ በማንነት ሳይለይ ሁሉንም ኦሮሞ መኅበረሰብ እኩል የሚደያርግ የአንድነት የእኩልነት መግለጫ ባህል መሆኑን ጥናት አቅራቢው አስረድተዋል፡፡አቶ ስንታየሁ በመጨረሻም ይህ የኦሮሞን ህዝብ አንድ ያደረገ የኢሬቻ እሴት በመወስድ ለኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ግንባታ ልናውለው ይገባል ሲሉ መክረዋል፡፡በደማቅ ሥነስርዓት የተከበረው የኢሬቻ የሠላም ሽልማት 1200 በላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመውታል፡፡   

 The summer trainees will graduate

It was announced that Ethiopia National cultural Center’s will graduate special summer trainees, who were trained by center for two months, in September 03, 2018 morning in the compound.

                         From left to right the trainees attending theoretical part and practice it on the stage

The center gave the training for 138 trainees in theatre, cultural dance, literature and drawing fields by volunteer trainers. Senior Artist Almtsehay Wodajo who was recent comer from USA to Ethiopia and other respected guests suppose to attend the graduation ceremony. It was known that the aims of the training were to transmit real country’s diverse cultures to the trainees, aware their truth culture and make them Culture ambassadors.       

 Cultural Expo opened In Ethiopian National Cultural Center compound 

Tuesday, august 28, 2018

In opening cultural expo speech, made yesterday in the Ethiopia National Cultural Center compound, announced that the first cultural expo has contribution to create market linkage, promotion culture and for encourage experts engage in the cultural sectors.

Handcraft articles present for visit and sale

According to EPRDF ministry of Culture Tourism minister Miss Fozia Amin said, among the started work, after Ethiopia Cultural Center started journey for reform to achieve being national’s cultural center, showing this cultural expo is part of reform plan.

From left to right EFDR ‘s ministry of Culture tourism minister Miss Fozia Amin made opening speech and Industry Minister D.R Ambachw Mekonnen ,Head’s of the center Tesfay Shimels together with other respected guests attending speech

Moreover, minister told that cultural expo has a great role to strength people to people relations, create market linkage and promotion.The Ministry of Culture tourism state minister of culture Miss Bizunesh Meseret, in her part, said that the first national expo uses to enhance products of culture and encourage in the sector. Remerging study, promotion and enrich the cultural values and features of the national, Nationalities and peoples of Ethiopia as center establishment objective EPRDF’s Industry Minister ,the day guest, D.R Ambachw Mekonnen said that expo, by encouraging handcraft articles, assists transformation to industrialization.

From left to right EFDR’s Industry Minister D.R Ambachw Mekonnen made speech Patriots and other respected guests attending speech

Appreciation the center reform, Ambachw said expo Preparation help the Communities’ to know their culture, pride on it and to use the product of it.Besides promotion cultural values for world, D.R said cultural expo has contribution for tourism sector. He suggested that the associations engaged in the sector to be assisted.In presence olds, patriots, cultural associations and concerned bodies cultural expo opened yesterday and stay until 9 November, 2018.

የባህል ኤክስፖ ሊከፈት ነው       

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል በአይነቱ የመጀመሪያው የሆነ የባህል ኤክስፖ/ዓውደ ርዕይ/ ከማክሰኞ ነሐሴ 22 ቀን 2010 በማዕከሉ ቅጥር ግቢ እንደሚከፍት አስታወቀ፡፡ 

 ከግራ ወደቀኝ የባህል ሽመናና የቃጫ ውጤቶች 

 በባህል ኤክስፖ/ዓውደ ርዕዩም/ የሀገራቱን ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በርካታ ባህላዊ የዕደ ጥበብና የኪነጥበብ ሥራዎች እንዲሁም ሌሎች ባህላዊ እሴቶቻችን ለእይታና ለሽያጭ በአንድ ግቢ ውስጥ ለታዳሚ እንደሚቀርብበት ታውቋል፡፡

 ከግራ ወደቀኝ ባህላዊ የሸማ መሣሪያና የቀርቀሃ ምርቶች 

በዝግጅቱ የተለያዩ አደረጃጀቶች የተሰማሩ የዘርፉ ማህበራት የሚሳተፉበትና ባህላዊ ቁሶችን በማቅረብ የትውውቅ እንዲሁም የገበያ ትስስር እድል ለመፍጠር ታስቧል፡፡ ኤክስፖ/አውደ ርዕዩ/ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣የዘርፉ ባለሙያዎች፣በርካታ እንግዶችና ተሳታፊዎች በሚገኙበት ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በይፋ በቅጥር ግቢው እንደሚከፈት ተነግሯል፡፡ አውደ ርኢይውን ለመታደም መግቢያ ዋጋ በነጻ እንደሆነም የታወቀ ሲሆን እስከ ጥቅምት መጨረሻ ዝግጅቱ እንደሚቆይ ተረጋግጧል፡፡

  የቡሔ በዓል በድምቀት ተከበረ 

         የቡሔ በዓል ትውፊቱን በጠበቀና የበዓሉን መገለጫዎች በሚያሳይ መልኩ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባህል ማዕከል ግቢ ነሐሴ 12 ቀን 2010 ዓ.ም ተከበረ፡፡

ከግራ ወደቀኝ የቡሔ ጭፈራና የጅራፍ ማጮህ በማዕከሉ ቅጥር ግቢ

በእለቱ የጅራፍ ገመዳና ማጮህ፣የሙልሙል ጋገራ፣የቡሔ ጭፈራ የችቦ ማብራት እንዲሁም የባህሉን ትውፊት የሚገልጹ የግጥም ድራማና የጥናታዊ ጹሁፍ ቀርበዋል፡፡

ከግራ ወደቀኝ በዓሉን አስመልክቶ የተዘጋጀውን ጭውውት የማዕከሉ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ሽመልስና ታዳሚዎች ዝግጅቱን ሲከታተሉ

ተጨማሪ ያንብቡ

  ጥሪ የተደረገላቸው አረጋዊያን በማዕከሉ አዳራሽ ዝግጅቱን ሲከታተሉ 

የቡሄ በዓል ከነሐሴ 12 2010 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮዽያ ብሔራዊ ባህል ማዕከል ይከበራል

ተጨማሪ ያንብቡ 

 ቡሄ በሉ… ልጆች ሁሉ

የደብረ ታቦር ወይም የቡሄ ወይም የሆያ ሆዬ ጨዋታ በአንድ አካባቢ ወይም በአንድ ጐጥ የሚኖሩ ልጆች ተሰባስበው በአካባቢያቸው የሚገኙትን ቤቶች እየዞሩ ማታ ላይ የሚያዜሙት የጨዋታ ዓይነት ነው፡፡ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎችና ከተሞች ከነሐሴ12 ወይም 13 ጀምሮ እስከ መስቀል/መስከረም 17 ድረስ ባሉት ቀናት የሚደረግ ጨዋታ ሲሆን በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ የቡሄ በዓል ቀን /ነሐሴ 13/ ብቻ ሆያ ሆዬ ጨዋታን ይጫወታሉ፡፡ሆያ ሆዬ በወንዶች ብቻ የሚቀርብ ጨዋታ ሲሆን ዜማውና ግጥሙ የገጠሩ አካባቢ ከከተማው ለየት ያለ ነው፡፡ የቡሄ ጨዋታ በአመዛኙ ሃይማኖታዊ መሠረት ኖሮት የሚከበር በዓል ሲሆን፤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት የደብረ ታቦር ምስጢር ጋር ተያይዞ የሚከበር ሃይማኖታዊ በዓል ነው፡፡

 በአሸንድየ ሻደይ፣ ሶለልና አሸንዳ ባህላዊ አለባበስ እና አጨፋፈር

በአሸንድዬ ፣ሻደይ፣ሶለልና አሸንዳ  በዓል ሴቶች በአንድ ላይ በመሰብሰብ የአሸንድየን ተክል ቆርጠው ያመጡና በወገባቸው ከሚታጠቁት ገመድ ላይ በስርዓት አቀጣጥለው በጉንጉን መልክ ያሰሩታል፡፡ ይህ የአሸንድዬ ተክል አብዛኛውን ጊዜ የሚገኘው ዳገታማ ከሆኑ ቦታዎች ነው፡፡ እናም በአንድ አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች ልጆች አሸንድያቸውን ታጥቀው፣ በተለያዩ ባህላዊ ልብሶች አጊጠው፤ፀጉራቸውን በተለያዩ የአሰራር አይነቶች ተውበው (ያገባችና ያላገባች)፣ በአካባቢያቸው ያሉትን መንደሮች እየዞሩ የታጠቁትን አሸንድዬ ወደ ግራ ወደ ቀኝ እያወዛወዙ የተለያዩ ዜማዎችን እያዜሙ አሸንድዬ ይላሉ፡፡በየ መንደሩ ካሉ ቤቶችም እየዞሩ በሚያዜሙበት ወቅት የቤቱን ባለቤት ስም እያነሱ ያወድሳሉ፡፡ የአሸንድዬ በዓል  በድምቀት  በአማራ ክልል በሰቆጣ (ዋግህምራ)፣ላስታ ላሊበላ፣መቄትና አብዛኛው በሰ/ወሎ አካባቢ ባሉት ወረዳዎች ይከበራል፡፡ በትግራይ ክልልም ተንቤን፣ራያ ዘቦ አካባቢዎችና በሌሎችም ይከበራል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

ባህላዊ መድሀኒቶቻችን 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማእከል ““የኢትዮጵያ ባህላዊ መዳኃኒቶች ከየት ወደ የት” በሚል መሪ ቃል ነሐሴ 04 ቀን 2010 ዓ.ም. በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የመሰብሰቢያ አዳራሽ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡የጥናቱ ዋና አለማ በሀገሪቱ ያለውን የባህል መዳህኒቶች ቅመማና አጠቃቀም ለዘመናዊ ህክምና የሚኖራቸውን ሚናን በመለየት በቀጣይም ባህላዊ መድኃኒቶች ለበለጠ ማህበራዊ ምጣኔ ሀበት እንዲውሉ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው ተግባራት የጋራ ሃሳቦችን በመውሰድና ክፍተቶችን እንዲሟሉ ለማድረግ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በውይቱ ከፋርማሲ ትምህርት ቤት ተለይተው ከመጡ፣ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ የክልልና የከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊዎች፣ በባህል ህክምና ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ በመድረኩ የጥናተዊ ጹሁፍ  እና የምክክር የአውደ ርዕይ ምልከታ እንደተካተተ ተረጋግጧል፡፡       

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል በማዕከሉ ንድፈ ዲዛይን ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በ03/12/2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

በመድረኩም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት፣ የክልሎች የባህል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊዎች፣ የክልል የባህል ማዕከል ኃላፊዎች፣ አርክቴክቶች፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራኖች፣ የሙያ ማህበራትና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡በዕለቱም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር የባህል ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ለተሳታፊዎች የመጀመሪያ ንድፍ ዲዛይኑ ሲቀርብ ሀሳቦች ተንሸራሽረው መካተት ያለበት ነገር ከእናንተ በግብአትነት ተሰጥቶ ዳብሮ አንድ ባህል ማዕከል መያዝ ያለበት ሀገራዊ ትውፊትን ለማሳደግ የሚችል ኢትዮጵያ ያላትን ባህል ሊያንፀባርቅ የሚችል ባህል ማዕከል በመገንባት ለትውልድ ቋሚ ነገርን ለማስረከብ ስለሆነ ያላችሁን ሙያዊ ዕውቀት ሳትሰስቱ እንድትሰጡን በማለት ውይይቱን አስጀምረዋል፡፡

አርክቴክት አርአያ የባህል ማዕከሉ የመጀመሪያ ንድፈ ህንፃ ለተሳታፊው ሲያቀርቡ

ከተሳታፊዎችም የተነሱ ጥያቄዎች የሚገነባው የባህል ማዕከል ኢትዮጵያን የሚገልፅ መሆን አለበት፣ ስለባህል ማዕከሉ ዝርዝር ይዘት ሳይነገረን ቀጥታ ወደ ዲዛይኑ መገባት አልነበረበትም፣ ስራው ለአንድ ባለሙያ ብቻ ከሚሰጥ ማወዳደር ለምን አልተቻለም ተወዳድሮ ቢሆን ኖሮ በርካታ ሃሳቦችም ሊመጡና በመጨረሻም ጨምቆ አንድ የባህል ማዕከል ምን መያዝ እንዳለበት መለየት ይቻል ነበር፣ በቅድሚያ የፕሮግራም መርሀ ገብር /TOR/ መዘጋጀት ነበረበት፣ ይዘቱ በአቅጣጫ የተከፋፈለ ጥናት መደረግ ነበረበት፣ ከአየር ንብረት እና ከአኗኗር አንፃር ጥናት መደረግ ነበረበት፣ በሀገራችን የስነ-ህንፃ ዘርፍ ጥበብ ስላለን ከዚያ አንፃር ጥናት መደረግ አለበት፣ የህንፃው ዲዛይን ሐበሻ ሐበሻ አይሸትም እንዲሸት ቢደረግ፣ ከውጪው ጀምሮ እኛን ሳይገልፅ ውስጡ ይገልፀናል ማለት አንችልም፣ በዚህ ዙሪያ ሁሉም ሰው ያገባዋል እና የምንሰራው ነገር ምንድነው የሚለውን ልምዱ ባላቸው ሰዎች ቢጠና፣ ቦታውንና የመሬት አቀማመጡን ጥናት ቢሰራ፣ ብሄረሰቦችን የሚወክል ነገር ሊኖረው ይገባል የሚሉ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ተነስተዋል፡፡ አርክቴክቱም የመጀመሪያ ዲዛይኑ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ድርጅቱ የተሰጠው የባህል ማዕከል ሳይሆን የመሰብሰቢያ አዳራሽ እና የምርምር ተቋም ዲዛይን እንዲሰሩ እንተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም ሚኒስትር ዴኤታዋ ክብርት ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት ይህ መድረክ ሲዘጋጅ የተሻለ ግብአት ለማግኘት በመሆኑ ተሳታፊዎችን አመስግነው፡፡በዚህ መድረክ የተነሱ ሃሳቦችንና አስተያየቶችን በማካተት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ዲዛይን ግንባታ ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል የውይይት መድረኮችን አዘጋጀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል የኢትዮጵያ ባህላዊ መድኃኒቶች ከየት ወደ የት በሚል መሪ ቃል ነሐሴ 04 ቀን 2010 ዓ.ም.በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የመሰብሰቢያ አዳራሽ የምክክር መድረክ እንደሚያደርግ እያስታወቀ፤ 

የጥናቱ ዋና አላማ በሀገሪቱ ያለውን የባህል መድኃኒቶች ቅመማና አጠቃቀም ለዘመናዊ ህክምና የሚኖራቸውን ሚና በመለየት በቀጣይም ባህላዊ መድኃኒቶች ለበለጠ ማህበራዊ ምጣኔ ሀበት እንዲውሉ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው ተግባራት የጋራ ሃሳቦችን በመውሰድና ክፍተቶችን እንዲሟሉ ለማድረግ እንደሆነ ታውቋል፡፡ 

በውይይቱ ከፋርማሲ ትምህርት ቤት ከተለዩት፣ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ የክልልና የከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊዎች፣ በባህል ህክምና ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች፣ ከህዝብ ክንፍ የተውጣጡ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 500 የሚሆኑ ተሳታፊዎች እንደሚካፈሉ ታውቋል፡፡በመድረኩ የጥናታዊ ጽሁፍ ላይ የምክክርና የአውደ ርዕይ ምልከታ እንደተካተተ ተረጋግጧል፡፡   

ተጨማሪ ያንብቡ

በተጨማሪም ማዕከሉ ነሐሴ 03 ቀን 2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል የማዕከሉን ህንጻ ለማስገንባት የመጀመሪያ የህንጻ ንድፍ ለማስተቸት መድረክ ያዘጋጃል፡፡

የመድረኩ ዋና አለማ ግንባታው የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ባህላዊ እሴቶችና መገለጫዎችን ለማበልጸግና ለማስተዋወቅ የሚችል የባህል ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል ግብዓት በማሰባሰብ ዋናውን የዲዛይን ስራ ለማስጀመር እንዲያስችል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሚደረግ ውይይት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

በመድረኩ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ክቡራን ሚንስትሮች እና ተጠሪ ተቋማት፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የባህል ማዕከላት ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎች እንዲሁም የህዝብ ክንፍና ታዋቂ ግለሰቦች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል በድሬዳዋ ከተማ የፎቶ ኤግዚቪሽን አሳየ፡፡ 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ድሬዳዋ ላይ በጠራው የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ የ2010 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ላይ የፎቶ ኤግዚቪሽን ፕሮግራም በማዘጋጀት በክቡራን ሚኒስተሮች ተከፍቶ በአካባቢው ነዋሪዎችና በተሳታዊዎች እንዲጎበኝ ተደርጓል፡፡ 

ከአባይ ተፋሰስ ሀገራት ጋር የባህል ትስስር ሊጀመር እንደሆነ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሽመልስ ተቋሙ በቅርብ የሚያከናውናቸውን ሥራዎች አስመልክቶ በማዕከሉ ሐምሌ 19/2010 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ሊሰሯቸው በዕቅድ የያዟቸውን ስራዎች አስመልክቶ የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሽመልስ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ፡፡

  • ከተነሱት ነጥቦችም ለ150 ወጣቶች በቲያትር፣በባህላዊ ውዝዋዜ እና በትውና በአንጋፋ አርቲስቶች ስልጠና መሰጠት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
  • ቡሄ በሉ ባህላዊ ቱፊቶችን ሳይለቅ በማዕከሉ ግቢ ውስጥ እንደሚዘጋጅ የተናገሩ ሲሆን ባህሉን ከሚገልጹ ክንውኖች ባሻገር የጥናታዊ ፁሁፎች እንደሚቀርብ አስታውቀዋል፡፡
  • ከአባይ ተፋሰስ የአፍሪካ ሀገራት ጋር የባህል ትስስር ለመፍጠር የባህል ሳምንት እንደሚካሄድ አስታውቀው ባህሉ ከጣና ባህርዳር ጀምሮ አዲስ አበባ እንደሚያልቅ ጠቁመዋል፡፡
  • የኢትዮ-ኤርትራ ህዝብ በባህል፣ በእምነት፣ በቋንቋ እና በስነልቦና የተሳሰረ ህዝብ እንደነበረ አስታውሰው አሁንም ሁለቱን ህዝቦች ያካተተ አውደ-ርዕይና የፓናል ውይይት እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡
  • አሸንዳ፣ አሸንድዩ እና ሶለን ባህላዊ ይዘት ያለው የህዝቦች እሴት አስመልክቶ በዓሉን በድምቀት በማዕከሉ የሚከበር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ባህሉን የሚያውቅ እንዲሁም በቋንቋው የሚኮራ ዜጋን ከመፍጠር አኳያ ማዕከሉ ሊሠራቸው ያሰበው ነገር ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ የሰጡት አቶ ተስፋዬ በእጃችን የነበሩንን መልካም ነገሮች የግጭት አፈታት ስርዓታችን፣ ኪነ ህንጻዎች፣ ለሃገር መሞት፣ እሴቶች ዋጅተናቸዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡አክለውም ሀገሪቱ የነበራትን መልካም እሴቶች ሳናውቅ አጥተናቸዋል ሠርተን እንመልሳቸዋለን ሲሉ መልስ ሰጥተዋል፡፡አቶ ተስፋዬ ሁሉም ባህሉን ለማበልጸግ ድርሻ እንዳለበት ተናግረው ማዕከሉ ድርሻውን ፖሊሲ በማውጣት እና ከማስተባበር ረገድ የሚመለከታቸው የድርሻቸውን እንደሚወጡ አስታውቀዋል፡፡ 

  በኢትዮዽያ ብሔራዊ ባህል ማዕከል  አዳራሽ  ከ18/11/2010 ዓ.ም ጀምሮ  ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ  ሰልጣኞች  በማዕከሉ ውዝዋዜ ና  ጥበብ ለማሰልጠን የመክፈቻ  ሥነ - ስርዓት  ሲከናወን

የኢትዮዽያ ብሔራዊ ባህል ማዕከል   ከ18/11/2010 ዓ.ም  በትያትር፣ በትወና እና በድርሰት ለሚሰጥ ስልጠና ከተለያዩ  ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ ሰልጣኞች የመክፈቻ  ሥነ - ስርዓት  ሲደረግ

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ፎዚያ አሚን እና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት በኢትዮጽያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ሰራተኞችን እና አመራሮችን በማዕከሉ በመገኘት ትውውቅ አድርገዋል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ፎዚያ አሚን ፤የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት ሐምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም በኢትዮጽያ ብሔራዊ የባህል ማዕከልን ሰራተኞች እና አመራሮች በማዕከሉ በመገኘት ትውውቅ አድርገዋል፡፡የማዕከሉ ተግባርና ሀላፊነት ላይ በጥልቀት ውይይት አካሂዷል፡፡ በተጨማሪም በማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ለበርካታ አመታት ተዘግተው የቆዩ አዳራሾችን በውስጣቸውም አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ በርካታ የዕደ ጥበብ ማሰልጠኛ መሳሪያዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በውይይቱም በማዕከሉ ባለፉት ዓመታት ስራዎች እየተሰሩ የቆዩ ቢሆንም እንደሌሎች የአለም ሀገራት የባህል ማዕከል የተሰጠውን ተልዕኮ ከማምጣት አኳያ የሰሯቸው ስራዎች በቂ ያልነበሩ እንደሆነ ከሰራተኞች በሰፊው የተነሱና በጥልቀት ውይይት የተካሄደበት ነው፡፡

የአዳራሽ ውይይት እንደተጠናቀቀም በግቢው ውስጥ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅትም የማዕከሉ ቅጥር ግቢ 42500 ካ.ሜ ስፋት ያለው ነገር ግን ውስጡ በአረም የተወረሰና ጫካ መሆኑን፤ የማዕከሉ ሰፊ አዳራሽ የሀገሪቱ ህገ መንግስት የጸደቀበት ለበርካታ ተቋማት በመሰብሰቢያነት አገልግሎት እየሰጠ የነበረና ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ሸራው ዝናብ እያስገባ አገልግሎት መስጠት ያቆመ በመሆኑ ለበርካታ ወራቶች ጥገና ሳያገኝ ቆይቷል፡፡ በዕደ ጥበብ ሙያ ላይ ልጣኞችን በመመልምል በቴክኖሎጂ የታገዘ ስልጠና መሰጠት ማዕከሉ የተሰጠው ተግባር ቢሆንም ለዚሁ አላማ የማሰልጠኛ ክፍሎችን ገንብቶ በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ስልጠናውን ለማስጀመር እንዲቻል የተለያዩ የማሰልጠኛ መሳሪያዎች ያሉ ቢሆንም ከአምስት ዓመት በላይ ምንም አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ መሆኑን ተመልክተዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በማዕከሉ እነዚህን ስራዎች ለማስጀመር እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ጎብኝተዋል ጅምር ስራዎችንም ማየትና ማረጋገጥም የቻሉ ሲሆን ከነዚህም በተለያዩ የዕደ-ጥበብና ኪነ-ጥበብ ሙያዎች ላይ በክረምት ወራት ሰልጣኞችን በማምጣት ስልጠናዎች ለመስጠት ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ት/ት ቤቶች ጋር በመወያየት ስራ ለማስጀመር እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡

በአጠቃላይ ባለፉት ዓመታት በርካታ የስራ እድል መፍጠር የሚችልበትን ነገር ግን ማዕከሉ መስራት የነበረበትን ያልሰራና ተልዕኮውን በበቂ መወጣት ያልቻለ መሆኑን በውይይቱ የተነሳውን በተግባር ያረጋገጡ ሲሆን አሁን እየተደረጉ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውና ማዕከሉን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡

ወቅታዊ እና ሀገራዊ ፋይዳ ያለው የውይይት መድረክ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ሰኔ 27 እና 28 /2010 ዓ.ም “የባህል ማዕከላት ሚና ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ” /በፕሮፌሰር በቀለ መኮንን/ እንዲሁም “በኢትዮጵያ ፊልሞች ውስጥ ኢትዮጵያዊነት አለን?” /በመስኩ ምሁራን/ በሚሉ ርዕሶች ላይ ወቅታዊና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ውይይቶች በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ሆቴል ያዘጋጃል ፡፡

በውይይቱም ክብርት ፎዚያ አሚን የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ሚንስትር፣ ጥሪ የተደረገላቸው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህል ቱሪዝምና የመገናኛ ብዙሀን ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊዎችና ባለሞያዎች፣ የባህል ሙያ ማህበራት ኃላፊዎችና አባላት፣ የተለያዮ የፌዴራል ተቋማት ተወካዮች፣ የሚዲያ አካላት፣ የሀይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የመንግስት የስራ ሀላፊዎች የሚገኙበት ሲሆን በሚያደርጉት ውይይትም ታላቅ ሀገራዊ መግባባት ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡                           

 የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ‹‹ የባህል ማዕከላት ሚና ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ›› በሚል ርዕስ ዛሬ ሰኔ 27/2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል ውይይት ተካሄደ ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ‹‹ የባህል ማዕከላት ሚና ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ›› በሚል ርዕስ ዛሬ ሰኔ 27/2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል ውይይት ተካሄደ ፡፡ በዝግጅቱም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ፎዚያ አሚን፤ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የባህል ቱሪዝምና የመገናኛ ብዙሀን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፤ የክልሎች እና የከተማ መስተዳደር የባህልና ቱሪዝም ቢሮዎችና የባህል ማዕከላት አመራሮች፤ የመስኩ ባለሙያዎች ፤ የጥበብ ቤተሰቦች በርካታ ተሳታፊዎች በተገኙበት በተባባሪ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን የመነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

 ከተሳታፊዎች በከፊል

   የቡሔ በዓል በድምቀት ተከበረ

     የቡሔ በዓል ትውፊቱን በጠበቀና የበዓሉን መገለጫዎች በሚያሳይ መልኩ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባህል ማዕከል ግቢ ነሐሴ 12 ቀን 2010 ዓ.ም ተከበረ፡፡

ከግራ ወደቀኝ የቡሔ ጭፈራና የጅራፍ ማጮህ በማዕከሉ ቅጥር ግቢ

በእለቱ የጅራፍ ገመዳና ማጮህ፣የሙልሙል ጋገራ፣የቡሔ ጭፈራ የችቦ ማብራት እንዲሁም የባህሉን ትውፊት የሚገልጹ የግጥም ድራማና የጥናታዊ ጹሁፍ ቀርበዋል፡፡

ከግራ ወደቀኝ በዓሉን አስመልክቶ የተዘጋጀውን ጭውውት የማዕከሉ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ሽመልስና ታዳሚዎች ዝግጅቱን ሲከታተሉ

ተጨማሪ ያንብቡ

  ጥሪ የተደረገላቸው አረጋዊያን በማዕከሉ አዳራሽ ዝግጅቱን ሲከታተሉ 

የቡሄ በዓል ከነሐሴ 12 2010 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮዽያ ብሔራዊ ባህል ማዕከል ይከበራል

ተጨማሪ ያንብቡ 

 ቡሄ በሉ… ልጆች ሁሉ

የደብረ ታቦር ወይም የቡሄ ወይም የሆያ ሆዬ ጨዋታ በአንድ አካባቢ ወይም በአንድ ጐጥ የሚኖሩ ልጆች ተሰባስበው በአካባቢያቸው የሚገኙትን ቤቶች እየዞሩ ማታ ላይ የሚያዜሙት የጨዋታ ዓይነት ነው፡፡ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎችና ከተሞች ከነሐሴ12 ወይም 13 ጀምሮ እስከ መስቀል/መስከረም 17 ድረስ ባሉት ቀናት የሚደረግ ጨዋታ ሲሆን በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ የቡሄ በዓል ቀን /ነሐሴ 13/ ብቻ ሆያ ሆዬ ጨዋታን ይጫወታሉ፡፡ሆያ ሆዬ በወንዶች ብቻ የሚቀርብ ጨዋታ ሲሆን ዜማውና ግጥሙ የገጠሩ አካባቢ ከከተማው ለየት ያለ ነው፡፡ የቡሄ ጨዋታ በአመዛኙ ሃይማኖታዊ መሠረት ኖሮት የሚከበር በዓል ሲሆን፤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት የደብረ ታቦር ምስጢር ጋር ተያይዞ የሚከበር ሃይማኖታዊ በዓል ነው፡፡

 በአሸንድየ ሻደይ፣ ሶለልና አሸንዳ ባህላዊ አለባበስ እና አጨፋፈር

በአሸንድዬ ፣ሻደይ፣ሶለልና አሸንዳ  በዓል ሴቶች በአንድ ላይ በመሰብሰብ የአሸንድየን ተክል ቆርጠው ያመጡና በወገባቸው ከሚታጠቁት ገመድ ላይ በስርዓት አቀጣጥለው በጉንጉን መልክ ያሰሩታል፡፡ ይህ የአሸንድዬ ተክል አብዛኛውን ጊዜ የሚገኘው ዳገታማ ከሆኑ ቦታዎች ነው፡፡ እናም በአንድ አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች ልጆች አሸንድያቸውን ታጥቀው፣ በተለያዩ ባህላዊ ልብሶች አጊጠው፤ፀጉራቸውን በተለያዩ የአሰራር አይነቶች ተውበው (ያገባችና ያላገባች)፣ በአካባቢያቸው ያሉትን መንደሮች እየዞሩ የታጠቁትን አሸንድዬ ወደ ግራ ወደ ቀኝ እያወዛወዙ የተለያዩ ዜማዎችን እያዜሙ አሸንድዬ ይላሉ፡፡በየ መንደሩ ካሉ ቤቶችም እየዞሩ በሚያዜሙበት ወቅት የቤቱን ባለቤት ስም እያነሱ ያወድሳሉ፡፡ የአሸንድዬ በዓል  በድምቀት  በአማራ ክልል በሰቆጣ (ዋግህምራ)፣ላስታ ላሊበላ፣መቄትና አብዛኛው በሰ/ወሎ አካባቢ ባሉት ወረዳዎች ይከበራል፡፡ በትግራይ ክልልም ተንቤን፣ራያ ዘቦ አካባቢዎችና በሌሎችም ይከበራል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ 

ባህላዊ መድሀኒቶቻችን  

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማእከል ““የኢትዮጵያ ባህላዊ መዳኃኒቶች ከየት ወደ የት” በሚል መሪ ቃል ነሐሴ 04 ቀን 2010 ዓ.ም. በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የመሰብሰቢያ አዳራሽ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡የጥናቱ ዋና አለማ በሀገሪቱ ያለውን የባህል መዳህኒቶች ቅመማና አጠቃቀም ለዘመናዊ ህክምና የሚኖራቸውን ሚናን በመለየት በቀጣይም ባህላዊ መድኃኒቶች ለበለጠ ማህበራዊ ምጣኔ ሀበት እንዲውሉ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው ተግባራት የጋራ ሃሳቦችን በመውሰድና ክፍተቶችን እንዲሟሉ ለማድረግ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በውይቱ ከፋርማሲ ትምህርት ቤት ተለይተው ከመጡ፣ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ የክልልና የከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊዎች፣ በባህል ህክምና ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ በመድረኩ የጥናተዊ ጹሁፍ  እና የምክክር የአውደ ርዕይ ምልከታ እንደተካተተ ተረጋግጧል፡፡        

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል በማዕከሉ ንድፈ ዲዛይን ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በ03/12/2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

በመድረኩም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት፣ የክልሎች የባህል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊዎች፣ የክልል የባህል ማዕከል ኃላፊዎች፣ አርክቴክቶች፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራኖች፣ የሙያ ማህበራትና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡በዕለቱም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር የባህል ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ለተሳታፊዎች የመጀመሪያ ንድፍ ዲዛይኑ ሲቀርብ ሀሳቦች ተንሸራሽረው መካተት ያለበት ነገር ከእናንተ በግብአትነት ተሰጥቶ ዳብሮ አንድ ባህል ማዕከል መያዝ ያለበት ሀገራዊ ትውፊትን ለማሳደግ የሚችል ኢትዮጵያ ያላትን ባህል ሊያንፀባርቅ የሚችል ባህል ማዕከል በመገንባት ለትውልድ ቋሚ ነገርን ለማስረከብ ስለሆነ ያላችሁን ሙያዊ ዕውቀት ሳትሰስቱ እንድትሰጡን በማለት ውይይቱን አስጀምረዋል፡፡

አርክቴክት አርአያ የባህል ማዕከሉ የመጀመሪያ ንድፈ ህንፃ ለተሳታፊው ሲያቀርቡ

ከተሳታፊዎችም የተነሱ ጥያቄዎች የሚገነባው የባህል ማዕከል ኢትዮጵያን የሚገልፅ መሆን አለበት፣ ስለባህል ማዕከሉ ዝርዝር ይዘት ሳይነገረን ቀጥታ ወደ ዲዛይኑ መገባት አልነበረበትም፣ ስራው ለአንድ ባለሙያ ብቻ ከሚሰጥ ማወዳደር ለምን አልተቻለም ተወዳድሮ ቢሆን ኖሮ በርካታ ሃሳቦችም ሊመጡና በመጨረሻም ጨምቆ አንድ የባህል ማዕከል ምን መያዝ እንዳለበት መለየት ይቻል ነበር፣ በቅድሚያ የፕሮግራም መርሀ ገብር /TOR/ መዘጋጀት ነበረበት፣ ይዘቱ በአቅጣጫ የተከፋፈለ ጥናት መደረግ ነበረበት፣ ከአየር ንብረት እና ከአኗኗር አንፃር ጥናት መደረግ ነበረበት፣ በሀገራችን የስነ-ህንፃ ዘርፍ ጥበብ ስላለን ከዚያ አንፃር ጥናት መደረግ አለበት፣ የህንፃው ዲዛይን ሐበሻ ሐበሻ አይሸትም እንዲሸት ቢደረግ፣ ከውጪው ጀምሮ እኛን ሳይገልፅ ውስጡ ይገልፀናል ማለት አንችልም፣ በዚህ ዙሪያ ሁሉም ሰው ያገባዋል እና የምንሰራው ነገር ምንድነው የሚለውን ልምዱ ባላቸው ሰዎች ቢጠና፣ ቦታውንና የመሬት አቀማመጡን ጥናት ቢሰራ፣ ብሄረሰቦችን የሚወክል ነገር ሊኖረው ይገባል የሚሉ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ተነስተዋል፡፡ አርክቴክቱም የመጀመሪያ ዲዛይኑ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ድርጅቱ የተሰጠው የባህል ማዕከል ሳይሆን የመሰብሰቢያ አዳራሽ እና የምርምር ተቋም ዲዛይን እንዲሰሩ እንተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም ሚኒስትር ዴኤታዋ ክብርት ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት ይህ መድረክ ሲዘጋጅ የተሻለ ግብአት ለማግኘት በመሆኑ ተሳታፊዎችን አመስግነው፡፡በዚህ መድረክ የተነሱ ሃሳቦችንና አስተያየቶችን በማካተት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ዲዛይን ግንባታ ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል የውይይት መድረኮችን አዘጋጀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል የኢትዮጵያ ባህላዊ መድኃኒቶች ከየት ወደ የት በሚል መሪ ቃል ነሐሴ 04 ቀን 2010 ዓ.ም.በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የመሰብሰቢያ አዳራሽ የምክክር መድረክ እንደሚያደርግ እያስታወቀ፤ 

የጥናቱ ዋና አላማ በሀገሪቱ ያለውን የባህል መድኃኒቶች ቅመማና አጠቃቀም ለዘመናዊ ህክምና የሚኖራቸውን ሚና በመለየት በቀጣይም ባህላዊ መድኃኒቶች ለበለጠ ማህበራዊ ምጣኔ ሀበት እንዲውሉ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው ተግባራት የጋራ ሃሳቦችን በመውሰድና ክፍተቶችን እንዲሟሉ ለማድረግ እንደሆነ ታውቋል፡፡ 

በውይይቱ ከፋርማሲ ትምህርት ቤት ከተለዩት፣ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ የክልልና የከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊዎች፣ በባህል ህክምና ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች፣ ከህዝብ ክንፍ የተውጣጡ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 500 የሚሆኑ ተሳታፊዎች እንደሚካፈሉ ታውቋል፡፡በመድረኩ የጥናታዊ ጽሁፍ ላይ የምክክርና የአውደ ርዕይ ምልከታ እንደተካተተ ተረጋግጧል፡፡   

ተጨማሪ ያንብቡ

በተጨማሪም ማዕከሉ ነሐሴ 03 ቀን 2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል የማዕከሉን ህንጻ ለማስገንባት የመጀመሪያ የህንጻ ንድፍ ለማስተቸት መድረክ ያዘጋጃል፡፡

የመድረኩ ዋና አለማ ግንባታው የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ባህላዊ እሴቶችና መገለጫዎችን ለማበልጸግና ለማስተዋወቅ የሚችል የባህል ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል ግብዓት በማሰባሰብ ዋናውን የዲዛይን ስራ ለማስጀመር እንዲያስችል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሚደረግ ውይይት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

በመድረኩ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ክቡራን ሚንስትሮች እና ተጠሪ ተቋማት፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የባህል ማዕከላት ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎች እንዲሁም የህዝብ ክንፍና ታዋቂ ግለሰቦች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል በድሬዳዋ ከተማ የፎቶ ኤግዚቪሽን አሳየ፡፡  

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ድሬዳዋ ላይ በጠራው የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ የ2010 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ላይ የፎቶ ኤግዚቪሽን ፕሮግራም በማዘጋጀት በክቡራን ሚኒስተሮች ተከፍቶ በአካባቢው ነዋሪዎችና በተሳታዊዎች እንዲጎበኝ ተደርጓል፡፡ 

ከአባይ ተፋሰስ ሀገራት ጋር የባህል ትስስር ሊጀመር እንደሆነ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሽመልስ ተቋሙ በቅርብ የሚያከናውናቸውን ሥራዎች አስመልክቶ በማዕከሉ ሐምሌ 19/2010 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ሊሰሯቸው በዕቅድ የያዟቸውን ስራዎች አስመልክቶ የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሽመልስ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ፡፡

  • ከተነሱት ነጥቦችም ለ150 ወጣቶች በቲያትር፣በባህላዊ ውዝዋዜ እና በትውና በአንጋፋ አርቲስቶች ስልጠና መሰጠት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
  • ቡሄ በሉ ባህላዊ ቱፊቶችን ሳይለቅ በማዕከሉ ግቢ ውስጥ እንደሚዘጋጅ የተናገሩ ሲሆን ባህሉን ከሚገልጹ ክንውኖች ባሻገር የጥናታዊ ፁሁፎች እንደሚቀርብ አስታውቀዋል፡፡
  • ከአባይ ተፋሰስ የአፍሪካ ሀገራት ጋር የባህል ትስስር ለመፍጠር የባህል ሳምንት እንደሚካሄድ አስታውቀው ባህሉ ከጣና ባህርዳር ጀምሮ አዲስ አበባ እንደሚያልቅ ጠቁመዋል፡፡
  • የኢትዮ-ኤርትራ ህዝብ በባህል፣ በእምነት፣ በቋንቋ እና በስነልቦና የተሳሰረ ህዝብ እንደነበረ አስታውሰው አሁንም ሁለቱን ህዝቦች ያካተተ አውደ-ርዕይና የፓናል ውይይት እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡
  • አሸንዳ፣ አሸንድዩ እና ሶለን ባህላዊ ይዘት ያለው የህዝቦች እሴት አስመልክቶ በዓሉን በድምቀት በማዕከሉ የሚከበር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ባህሉን የሚያውቅ እንዲሁም በቋንቋው የሚኮራ ዜጋን ከመፍጠር አኳያ ማዕከሉ ሊሠራቸው ያሰበው ነገር ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ የሰጡት አቶ ተስፋዬ በእጃችን የነበሩንን መልካም ነገሮች የግጭት አፈታት ስርዓታችን፣ ኪነ ህንጻዎች፣ ለሃገር መሞት፣ እሴቶች ዋጅተናቸዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡አክለውም ሀገሪቱ የነበራትን መልካም እሴቶች ሳናውቅ አጥተናቸዋል ሠርተን እንመልሳቸዋለን ሲሉ መልስ ሰጥተዋል፡፡አቶ ተስፋዬ ሁሉም ባህሉን ለማበልጸግ ድርሻ እንዳለበት ተናግረው ማዕከሉ ድርሻውን ፖሊሲ በማውጣት እና ከማስተባበር ረገድ የሚመለከታቸው የድርሻቸውን እንደሚወጡ አስታውቀዋል፡፡ 

በኢትዮዽያ ብሔራዊ ባህል ማዕከል  አዳራሽ  ከ18/11/2010 ዓ.ም ጀምሮ  ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ  ሰልጣኞች  በማዕከሉ ውዝዋዜ ና  ጥበብ ለማሰልጠን የመክፈቻ  ሥነ - ስርዓት  ሲከናወን

  የኢትዮዽያ ብሔራዊ ባህል ማዕከል   ከ18/11/2010 ዓ.ም  በትያትር፣ በትወና  እና በድርሰት ለሚሰጥ ስልጠና ከተለያዩ  ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ ሰልጣኞች የመክፈቻ  ሥነ - ስርዓት  ሲደረግ

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ፎዚያ አሚን እና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት በኢትዮጽያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ሰራተኞችን እና አመራሮችን በማዕከሉ በመገኘት ትውውቅ አድርገዋል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ፎዚያ አሚን ፤የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት ሐምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም በኢትዮጽያ ብሔራዊ የባህል ማዕከልን ሰራተኞች እና አመራሮች በማዕከሉ በመገኘት ትውውቅ አድርገዋል፡፡የማዕከሉ ተግባርና ሀላፊነት ላይ በጥልቀት ውይይት አካሂዷል፡፡ በተጨማሪም በማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ለበርካታ አመታት ተዘግተው የቆዩ አዳራሾችን በውስጣቸውም አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ በርካታ የዕደ ጥበብ ማሰልጠኛ መሳሪያዎችን ጎብኝተዋል፡፡ 

በውይይቱም በማዕከሉ ባለፉት ዓመታት ስራዎች እየተሰሩ የቆዩ ቢሆንም እንደሌሎች የአለም ሀገራት የባህል ማዕከል የተሰጠውን ተልዕኮ ከማምጣት አኳያ የሰሯቸው ስራዎች በቂ ያልነበሩ እንደሆነ ከሰራተኞች በሰፊው የተነሱና በጥልቀት ውይይት የተካሄደበት ነው፡፡

የአዳራሽ ውይይት እንደተጠናቀቀም በግቢው ውስጥ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅትም የማዕከሉ ቅጥር ግቢ 42500 ካ.ሜ ስፋት ያለው ነገር ግን ውስጡ በአረም የተወረሰና ጫካ መሆኑን፤ የማዕከሉ ሰፊ አዳራሽ የሀገሪቱ ህገ መንግስት የጸደቀበት ለበርካታ ተቋማት በመሰብሰቢያነት አገልግሎት እየሰጠ የነበረና ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ሸራው ዝናብ እያስገባ አገልግሎት መስጠት ያቆመ በመሆኑ ለበርካታ ወራቶች ጥገና ሳያገኝ ቆይቷል፡፡ በዕደ ጥበብ ሙያ ላይ ልጣኞችን በመመልምል በቴክኖሎጂ የታገዘ ስልጠና መሰጠት ማዕከሉ የተሰጠው ተግባር ቢሆንም ለዚሁ አላማ የማሰልጠኛ ክፍሎችን ገንብቶ በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ስልጠናውን ለማስጀመር እንዲቻል የተለያዩ የማሰልጠኛ መሳሪያዎች ያሉ ቢሆንም ከአምስት ዓመት በላይ ምንም አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ መሆኑን ተመልክተዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በማዕከሉ እነዚህን ስራዎች ለማስጀመር እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ጎብኝተዋል ጅምር ስራዎችንም ማየትና ማረጋገጥም የቻሉ ሲሆን ከነዚህም በተለያዩ የዕደ-ጥበብና ኪነ-ጥበብ ሙያዎች ላይ በክረምት ወራት ሰልጣኞችን በማምጣት ስልጠናዎች ለመስጠት ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ት/ት ቤቶች ጋር በመወያየት ስራ ለማስጀመር እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡

በአጠቃላይ ባለፉት ዓመታት በርካታ የስራ እድል መፍጠር የሚችልበትን ነገር ግን ማዕከሉ መስራት የነበረበትን ያልሰራና ተልዕኮውን በበቂ መወጣት ያልቻለ መሆኑን በውይይቱ የተነሳውን በተግባር ያረጋገጡ ሲሆን አሁን እየተደረጉ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውና ማዕከሉን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ እና ሀገራዊ ፋይዳ ያለው የውይይት መድረክ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ሰኔ 27 እና 28 /2010 ዓ.ም የባህል ማዕከላት ሚና ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ/በፕሮፌሰር በቀለ መኮንን/ እንዲሁም በኢትዮጵያ ፊልሞች ውስጥ ኢትዮጵያዊነት አለን?” /በመስኩ ምሁራን/ በሚሉ ርዕሶች ላይ ወቅታዊና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ውይይቶች በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ሆቴል ያዘጋጃል ፡፡

በውይይቱም ክብርት ፎዚያ አሚን የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ሚንስትር፣ ጥሪ የተደረገላቸው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህል ቱሪዝምና የመገናኛ ብዙሀን ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊዎችና ባለሞያዎች፣ የባህል ሙያ ማህበራት ኃላፊዎችና አባላት፣ የተለያዮ የፌዴራል ተቋማት ተወካዮች፣ የሚዲያ አካላት፣ የሀይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የመንግስት የስራ ሀላፊዎች የሚገኙበት ሲሆን በሚያደርጉት ውይይትም ታላቅ ሀገራዊ መግባባት ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡                           

 የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ‹‹ የባህል ማዕከላት ሚና ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ›› በሚል ርዕስ ዛሬ ሰኔ 27/2010 . በኢትዮጵያ ሆቴል ውይይት ተካሄደ ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ‹‹ የባህል ማዕከላት ሚና ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ›› በሚል ርዕስ ዛሬ ሰኔ 27/2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል ውይይት ተካሄደ ፡፡ በዝግጅቱም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ፎዚያ አሚን፤ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የባህል ቱሪዝምና የመገናኛ ብዙሀን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፤ የክልሎች እና የከተማ መስተዳደር የባህልና ቱሪዝም ቢሮዎችና የባህል ማዕከላት አመራሮች፤  የመስኩባለሙያዎች ፤ የጥበብ ቤተሰቦች በርካታ ተሳታፊዎች በተገኙበት በተባባሪ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን የመነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

                ከተሳታፊዎች በከፊል